ባማላኩ ጨክኖ
“ስቅሎ ስቅሎ” ብሎ እንዳላሰቀለ
አይ ሰው ወበከንቱ
ለመሰሉ ቢሆን
አውርደው፡ አውርደው ወጣ ካንደበቱ፤፤
አጃኢብ ነው’ኮ አጀብ የሰው ነገር
ላያወርድ ሲሰቅል ላይሰቅል ሲያወርድ
ፈጣሪው ሰቅሎ ፍጡሩን ሲማለድ
ሊፈጸም ካልሆነ
ስቀለው አይሰቅል ና ውረድ አያወርድ፤፤
መጀመሪያ ነበረ ‘ሚሰቅሉትን መለየት
ወይ ደግሞ
አሳጥሮ መስቀል
ካልሆነ ካልሆነ
መስቀያውን መቁረጥ፤፤
ኒዎርሊንስ-ሚያዝያ 2011 እ.ኤ. አ
No comments:
Post a Comment